Sunday, July 22, 2012

Wonderer Of The Skys, 21 July 2012.


የመንግስተ ሰማያት ፌዴሬሽን ።
በሰማይ መንገደኛ በኩል የተላከ ።
ሐምሌ ፩፬ ፪፼፬ ዓመተምሕረት ።

ከፌዴሬሽኑ ሰላምታ ይድረሳችሁ ፡
ለእናንተ ማመን አዳጋች ሊሆን ቢችልም፡ በአለማችሁ ላይ ለረጅም ጊዜ የታቀደውን ቅዱስ ውጥን በተግባር የሚያውሉ ድርጊቶች እየተካሄዱ ናቸው። እኛም በዚህ የጥርጣሬ ዘመን ወደ መሬት የመጣችሁበትን ጉዳይ በምታከናዉንበት ጊዜ አጠገባችሁ ለመገኘት መጥተናል። ማንነታችሁን እና ከየት እንደመጣችሁ የማስታወስ ችሎታ አለመኖሩ የፈጠረዉን አዳጋች ሁኔታ እንረዳለን። የእናንተ ሁኔታ ግድ ስለሚሰጠን እኛም እዚህ መጥተናል። በአለማችሁ መድረክ ላይ የተኪያሄዱትን እና ያልተኪያሄዱትን ተግባራት ሙሉ በሙሉ መረዳት ባትችሉም፡ እኛ እንላችኋለን፡ ሁላችሁም ከረጅም ጊዜ በፊት በታቀደው ውጥን መሠረት እየተራመዳችሁ ነው።
በቅርቡ በዜና ማሰራጫዎች ሊቃውንቶቻችሁ የለኩትን እና የታዘቡትን የአለማችሁን የኃይል ስርጭት ለውጥ ይፋ ያደርጋሉ። ይህም ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመስፋፋት ላይ ያለዉን እና አለማችሁ ከሚገኝበት የተጠላለፈ ሁኔታ የሚያላቅቀው ኃይል አካል ነው። በተለይም ለውጦች ግልፅ መሆን መጀመራቸዉን ልብ ካላችሁ፡ ይህ ኃይል አለማችሁ ላይ በማስከተል ላይ ያለዉን ለውጥ መረዳት ትችላላችሁ።

ሁሌም እንደተናገርነው፡ በአለማችሁ ላይ የሚካሄደው ለውጥ በመድረካዊ ትርኢት አይነት ሳይሆን ቀስ በቀስ የሚካሄዱ በስተመጨረሻም የታቀደውን ውጤት በሚያስገኙ ለውጦች ነው። እናንተ የምትጠብቁት በመንግስት በንዋይ ተቋሞች በምጣኔሃብት ከፍተኛ ለውጦችን ለማየት ሲሆን፡ ይህን አይነት ለውጥ ግን ለህዝቦቻችሁ ከአቅም በላይ የሆነ ማዳገትን ይፈጥራል። ስለዚህ እነዚህ ለውጦች እንደ ሌሎች አስፈላጊ ለውጦች ሁሉ ቀስ በቀስ የሚካሄዱ እና አንዳድ ጊዜም ጅምራቸውን ለማየት የሚያዳግቱ ናቸው። ይሁን እንጂ ለውጥ አለ፡ እየተካሄደም ነው። ህዝቦቻችሁ ለዘብ ባለ ግን ጉልበት በተሞላበት ለንዋይ ተቋማት ያላቸውን አመለካከት መለወጣቸዉን ልብ ብላችኋልን፧ በአለም ላይ የሚደርሰው የተፈጥሮ አደጋ እየቀነሰ መምጣቱን ልብ ብላችኋልን፧ የአለማችሁ መሪዎች የታላላቅ ኩባንያዎችን ጥቅም ሳይሆን የህዝብ ጥቅም በሚመለከቱ ጉዳዮች እና ጥያቄዎች ላይ ያላቸውን አመለካከት እየለወጡ መምጣታቸውን ልብ ብላችኋልን፧ እነዚህም ለዛባ ለውጦች በጉአዳ የሚደረጉት ዉሎች ድርድሮችና እንቅስቃሴዎች ውጤት ናቸው።

በቅርቡ በመንግሥተ ሠማያት ደረጃ፡ እስካሁን የተኪያሄደዉን እና ውጥኑን ከግብ ለማድረስ የሚቀሩትን ተግባራት ለማጤን ተሰባስበን ነበር። ይህም ስብሰባ እንደ ከዚህበፊቱ ከታላቅ የጠፈር መንኮራኩሮቻችን በአንዱ ላይ የተኪያሄደ ሲሆን፡ በጣም ተስማሚ መግባባቶች ላይ ተደርሷል። በዚህ ስብሰባ ላይ የአለማችሁ እና የመንግሥተ ሠማያት ተወካዮች ተካፍለዋል። ህዝቦቻችሁ ተሰሚነት አግኝተዋል፡ ያላችሁም ስሜት ለተደረሱት መግባባቶች መስረት ሆነዋል። በተደረሰው መግባባት መሰረት የመጀመሪያውን የምር እርምጃ መዉሰድ ጀምረናል። በዚህም የመጀመሪያ እርምጃ መሰረት በሰማያችሁ ላይ በብዛት አንዣበን መታየት እንጀምራለን። የዋናው ጉዳይ እንቅስቃሴ ተጀመረ።

ህዝቦቻችሁ የተገለፀላቸው በመባል የሚታወቁት ሴረኞች ምንያህል አለማችሁን አንቀው እንደሚቆጣጠሩ እየተረዱ መተዋል። ይህን ቁጥጥር ለማክሰም ችሎታ ያላቸው መሪዎች በአሁን ጊዜ እርምጃ መዉሰድ እንደሚችሉ እና ከሚስጥራዊ ሴረኞች በኩል የሚመጣ ተቃውሞ እየቀነሰ መምጣቱን እየተረዱ መተዋል። በእናንተ ጀግኖች ደፋር እንቅስቃሴ፡ እኛ በውጥኑ መሰረት በምንወስዳቸው የመጀመሪያ ተከታታይ እርምጃዎች፡ የአለማችሁን ኃይል ለሚቀጥለው እርከን በሚያበቃ ደረጃ ከፍ በማድረግ ለውጥኑ ተከታይ ክፍል ተግባራዊነት እንደምንደርስ እንተማመናለን።

እናንተ በጣም አስደናቂ ሰዎች ናችሁ። ለረጅም ጊዜ እና በታታሬነት በዚህ በመንግሥተ ሠማያት ከሚገኙት ሁሉ ታላቅ በሆነው መንፈሣዊ ትምሕርት ቤት ስትማሩ ቆይታችሁ አሁን ለምርቃት እየተዘጋጃችሁ ነው። እናንተ መስጠት የምትችሉት አገልግሎት በሠማየሠማያት ሁሉ በጉጉት ይጠበቃል፡ በምትሄዱበት ሁሉ ለደረሳችሁበት ደረጃ እና ለማንነታችሁ ከፍተኛ አድናቆት እና ከበሬታ በማሳየት ለመቀበል ሁሉም እጆቻቸዉን ዘርግተው ይጠብቋችኋል። ለተሳካ ውጤጥ በፍቅር እና በቆራጥነት ተገኙ። እኛም በበኩላችን የናንተን ችሎታ ጥበበኛነት እና ያልተገራ መንፈሣዊ ጉልበት ሁሌ እናደንቃለን።

ሰላም ከናንተ ይሁን።

ትርጉም ፡ ሰለሞን ደበበ